News and Press

ባንኩ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዝገቡ ቅርንጫፎች እና ዲስትሪክቶች እውቅና ሰጠ፡፡

ፀደይ ባንክ በ2024/2025 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዝገቡ ቅርንጫፎች እና ዲስትሪክቶች እውቅና ሰጥቷል፡፡

ፀደይ ባንክ የ2024/2025 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ አፈጻጸሙን በተመለከተ ከሰሞኑ ተወያይቷል፡፡ በዚህም የተለያዩ መመዘኛዎችን መሠረት በማድረግ የሁሉም ዲትሪክቶች እና ቅርንጫፎች አፈጻጸም ላይ ውይይት በማካሄድ በቀጣይ በትኩረት መፈጸም ያለባቸው ዐበይት ነጥቦችን አስቀምጧል፡፡

ይህን ተከትሎም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች እውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል፡፡

ደሴ፣ ወልድያ እና ሰቆጣ ዲስትሪክቶች የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከደሴ ዲስትሪክት፡- ዋርካ እና ፒያሳ፤ ከአዲስ አበባ ዲስትሪክት፡-አራት ኪሎ፤ ከፍኖተ ሠላም ዲስትሪክት፡- ብራቃት፤ ከደብረ ብርሃን ዲስትሪክት፡-  አጼ ሚኒልክ፤ ከሰቆጣ ዲስትሪክት፡- ተላጀ ሐሙሲት፤ ከደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት፡- ዋብር እንዲሁም ከደብረ ታቦር ዲስትሪክት፡- ጋፋት ቅርንጫፎች የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የምስክር ወቀረት የተበረከተላቸው ቅርንጫፎች ደግሞ፡- ከባሕር ዳር ዲስትሪክት፡- ጣና (3)፣ ዳግማዊ ሚኒልክ (3)፣ ባሕር ዳር (2)፣ ፍኖተ፣ ሰፈነ ሠላም እና ደንገል፤ ከደሴ ዲስትሪክት፡-ፒያሳ (2)፣ ወለዲ፣ ዋርካ፣ አዳሜ እና መቅደላ፤ ከአዲስ አበባ ዲስትሪክት፡- አራት ኪሎ (2)፣ ባልደራስ (2)፣ ቦሌ (2)፣ ወሎ ሰፈር (2) እና ሻላ፤ ከጎንደር ዲስትሪክት፡- ድማዛ (2) እና ጠለምት፤ ከደብረ ታቦር ዲስትሪክት፡- ጋፋት እና አለቃ ገብረሃና፤ ከሰቆጣ ዲስትሪክት፡- ተላጀ ሐሙሲት እና ፈረስ መጋለቢያ፤ ከፍኖተ ሠላም ዲስትሪክት፡- ቡሬ ዳሞት (2) እና ብራቃት፤ ከደብረ ብርሃን ዲስትሪክት፡- አጼ ሚኒልክ (2) እና ደነባ፤ ከእንጂባራ ዲስትሪክት፡- ወርቅ ሜዳ፣ አቫድራ እና አፈሳ፤ ከደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት፡- ቁይ እና ዋብር ቅርንጫፎች ናቸው፡፡

ፀደይ ባንክ በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ ሃብቱን 62 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ካፒታሉን ደግሞ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር አድርሷል፡፡

ከ14 ሚሊዮን በላይ አጠቃላይ ደንበኞቹ ያሉት ፀደይ ባንክ፣ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ለሚልቁ ደንበኞቹ ደግሞ ብድር በመስጠት ብዙዎችን ከህልማቸው ጋር አገናኝቷል፡፡

ተደራሽነቱን በመላ ሃገሪቱ በማስፋፋትም የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ627 በላይ አድርሷል፡፡

የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች የሽልማት አሰጣጥ በከፊል

የሁሉም ባንክ!
Bank for all!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *