የጨረታ ማስታዎቂያ
ፀደይ ባንክ (አ.ማ) ለአቶ ጌታቸው አባት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሰንጠረጁ
የተዘረዘሩ መኖሪያ ቤቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው
ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራጮች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራጮች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼(በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ
በፀደይ ባንክ ስም (አ.ማ) በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማሲያዝ በጨረታው መሳተፍ
ይችላሉ፡፡ - ለጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጹሁፍ
ወይም መተዳደሪያ ደንብ ፣ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት
እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት፡፡ - የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል
ፀድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡ - የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን
ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ
ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ
በሲ.ፒ.ኦ የአሲያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ - በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራጮች ያሲያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ
ክፍያዎች፤ ግብር እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች
ይከፍላሉ፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዡ
ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡ - ተጫራጮች ቤቶችን መስከረም 8 ቀን 2017ዓ.ም በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም
ማየት ይችላሉ፡፡ - በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ
ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡ - የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ለገሀር በሚገኘው የፀደይ ባንክ
አ.ማ ዋናው መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
10.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115584896 እና 0115581905 በመደወል መጠየቅ
ይቻላል፡፡

Leave a Reply