News and Press

የፀደይ ባንክ አትሌቶች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 5 ኪ.ሜ ውድድር አሸነፉ።

የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ አትሌቶች ዛሬ መጋቢት 07/2017 ዓ.ም በተካሄደው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል።

ውድድሩ በየዓመቱ የሚዘጋጅ፣ በርካታ ልምድ ያላቸው እና ጠንካራ ሴት አትሌቶች የሚሳተፉበት ነው።

በዚህ የ 5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ውድድር የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ አትሌት ብርነሽ ደሴ 1ኛ፣ አትሌት መቅደስ ሽመልስ ደግሞ 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል። በውድድሩ 2ኛ የወጣችው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌት አበዙ ከበደ ናት።

በዚህ ውድድር ባለፈው ዓመት አትሌት ብርነሽ ደሴ 2ኛ፣ አትሌት መቅደስ ሽመልስ ደግሞ 3ኛ በመውጣት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

በርካታ ማኅበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ የሚገኘው ፀደይ ባንክ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የራሱን አትሌቲክስ ክለብ በመመስረትና በጀት በመመደብ በርካታ ወጣት አትሌቶች ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉና ሀገርን በተለያዩ መድረኮች እንዲያስጠሩ እያደረገ ይገኛል።

የሁሉም ባንክ!
Bank for all!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *