የፀደይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የስብሰባ ጥሪ ማስታዎቂያ
ለፀደይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ!
የፀደይ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ቁጥር 1243/2023 አንቀፅ 366፣367፣370፣ 371 እና 372 መሠርት ቅዳሜ ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ባሕር ዳር በሚገኝው ብሉናይል (አቫንቲ) ሆቴል ይካሄዳል። ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት፣ እና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።
ሀ. የ2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡–
- አጀንዳዎቹን ማጽደቅ፣
- የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣
- እ.አ.አ የ2021/2022 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.አ.አ የ2021/2022 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተር ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ∙አ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት በተገኝ የተጣራ ትርፍ አደላደል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
- እ∙አ.አ የ2021/22 በጀት ዓመት በተገኝ የተጣራ ትርፍ አደላደል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
- እ.አ.አ የ2021/22 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን እና
- የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ናቸው።
ለ. የ2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች፡–
- የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
- የባንኩን ካፒታል ስለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ መወሰን እና ለተግባራዊነቱ ለዳይሬክተሮች ቦርድ ውክልና መስጠት፣
- የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል እና
- የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ ናቸው።
ማሳሰቢያ፡–
- ባለአክሲዮኖች በጉባኤው ለመገኘት ኢትዮጵያዊነታችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
- በስብሰባው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና (proxy) ቅጽ አዲስ አበባ ለገሃር አመልድ ሕንፃ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት፣ 8ኛ ፎቅ ወስዳችሁ በመሙላት ከስብሰባው ሦስት ቀናት በፊት ውክልና መስጠት እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡
- በውልና የምትሳተፉ ከሆነ ዋናውን የውክልና ሰነድና ኮፒ፣ ማንነታችሁን የሚያሳይ
ዋናውንና ኮፒ መታወቂያ እንዲሁም የወካያችሁን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵዊ መሆኑን የሚያሳይ ኮፒ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን። - በስብሰባው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖችና ተወካዮች እንዲሁም በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና (proxy) የምትሰጡ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
- ድርጅትን ወክሎ የሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ ወይም የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ወይም ቃለጉባዔ ይዞ መቅረብ ወይም በባንኩ የውክልና ቅጽ መሠረት ውክልና የተሰጠው መሆን አለበት፡፡
- የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻያ ሰነድ ከባንኩ ቅርንጫፎች እና የባንኩ ድረ ገጽ (https://tsedeybank-sc.com/) ላይ በማውረድ ማግኘት እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡
ስለባንኩ መግለጫ
- የባንኩ የተፈረመ ካፒታል፡- ብር 7,749,905,000
- የባንኩ የተከፈለ ካፒታል፡- ብር 7,749,905,000
- የባንኩ ዋና የንግድ ምዝገባ ቁጥር፡- MT/AA/3/0052707/2014
- የባንኩ የሥራ ፈቃድ ቁጥር፡- LLB/TM/026/2022
- አድራሻ፡-አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ለገሃር መብራት አካባቢ አመልድ ሕንጻ ከ07-14ኛ ፎቅ
- ድረ ገጽ፡- www.tsedeybank-sc.com
- ስልክ ቁጥር፡- 0115584133
- ፖ.ሣ.ቁ.፡- Box: 9630
- ኢ.ሜል፡- info@tsedeybank-sc.com
የፀደይ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ!
Leave a Reply