News and Press

ፀደይ ባንክ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸሙን አስመልክቶ በዋናው መሥሪያ ቤት  ምክክር አካሄደ፡፡

ፀደይ ባንክ በዲስትሪክቶች ደረጃ ሲያካሂድ የነበረውን የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ምክክር ዛሬ ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም በዋናው መሥሪያ ቤት አካሂዷል፡፡

ባንኩ የዲስትሪክቶችን አፈጻጸም ከሰሞኑ ሲገመግም ቆይቷል።

ዛሬ ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም ደግሞ በአፈጻጸሙ ላይ በዋናው መሥሪያ ቤት ደረጃ ውይይት አድርጓል፡፡ በምክክሩ የክፍል ሥራ አስኪያጆች፣ ዳይሬክተሮች እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ አሁን የተመዘገበውን የተሻሻለ አፈጻጸም ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ምክክር  አካሂዷል፡፡

በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገባቸው ነጥቦች ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡

ፀደይ ባንክ አጠቃላይ ሀብቱን 62 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ካፒታሉን ደግሞ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር አድርሷል፡፡

ከ14 ሚሊዮን በላይ አጠቃላይ ደንበኞች ያሉት ባንኩ፣ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ለሚልቁ ደንበኞቹ ብድር ሰጥቷል።

እንወዳጅ!

Telegram: https://t.me/tsedeybanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/tsedey-bank-s-c/
Facebook: https://www.facebook.com/TsedeyBankSC
TikTok: http://www.tiktok.com/@tsedeybanksc
Twitter: https://twitter.com/TsedeyBankSC
YouTube: https://youtube.com/@TsedeyBank

የሁሉም ባንክ!
Bank for all!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *