ፀደይ ባንክ የ2023/24 አፈፃፀም እና 2024/25 እቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ባንኩ የማኔጅመንት አባላት፣ የዲስትሪክት እና ዲቪዥን ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት ነው የአፈፃፀም እና የእቅድ ውይይቱን ዛሬ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም በዋና መሥሪያ ቤቱ ያካሄደው።
በውይይቱም የ2023/24 አፈፃፀሙን በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የ2024/25 እቅድ ላይም በስፋት ውይይት በማካሄድ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መግባባት ላይ ተደርሷል።
Leave a Reply