News and Press

የጨረታ ማስታዎቂያ

ፀደይ ባንክ (አ.ማ) ለአቶ ጌታቸው አባት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሰንጠረዡ የተዘረዘሩ መኖሪያ ቤቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራጮች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራጮች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፀደይ ባንክ ስም (አ.ማ) በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  5. በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
  7. ተጫራጮች ቤቶችን ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ቂርቆስ ክ.ከተማ ለገሀር በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ ዋናው መ.ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 558 48 96 እና 011 558 19 05 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የጨረታውን ዝርዝር መረጃዎች ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡- https://t.me/tsedeybanksc/980

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *