News and Press

ይህን ያውቁ ኖሯል !

የኤ ቲ ኤም አገልግሎት በበረዷማው አሕጉር ውስጥ መኖሩን ያውቃሉ!

ለመኖር እጅግ አስቸጋሪ በሆነው በበረዷማው አንታርክቲካ አሕጉር ውስጥ ሁለት የኤቲኤም ማሽኖች ይገኛሉ፡፡ የማሽኖቹ ባለቤት አሜሪካን ሀገር ሰን ፍራንሲስኮ የሚገኘው Wells Fargo የተባለ ባንክ ነው፡፡ አንታርክቲካ ውስጥ እንዲቀመጡና አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረጉት ደግሞ እ.አ.አ ከ1998 ጀምሮ ነው፡፡

ለሰው ልጆች ለመኖር እጅግ ፈታኝ በሆነው አሕጉር ውስጥ ላለፉት 25 ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ሁለቱ የኤቲኤም ማሽኖች የተገጠሙት ማክ ሙርዶ (Mc Murdo) በተባለ የሳይንስ ጣቢያ አካባቢ ነው፡፡

ማሽኖቹ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ደግሞ በአሜሪካን ዶላር እንደሆነ የኢንዲያን ታይምስ ዘገባ አመላክቷል፡፡ ተጠቃሚዎቹም በዋናነት ለምርምር ሥራ በአካባቢው የሚገኙ እና ለጉብኝት የሄዱ ሰዎች ናቸው፡፡

ኤ ቲ ኤም ማሽኖቹ ብልሽት ቢያጋጥማቸው ድርጅቱ ያሰለጠናቸው በአንታርክቲካ ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞቹ እንደሚያስተካክሉት ነው በዘገባው የተመላከተው፡፡

በተጨማሪም ማሽኖቹ በየሁለት ዓመቱ አጠቃላይ ፍተሻ እና ማስተካከያ ይደረግባቸዋል ይላል የኢንዲያን ታምስ መረጃ፡፡ በዚህ የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንደሚጫኑባቸውም ነው የተገለፀው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220