ፀደይ ባንክ እና ጤና ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ፡፡
ፀደይ ባንክ የዲጂታል ጤና ክፍያ የሙከራ ትግበራ ላይ በጋራ ለመሥራት ከጤና ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ የፊርማ ሥነ-ሥርዐቱ ዛሬ የካቲት 26/2017 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ ነው የተከናወነው፡፡
ስምምነቱን የፀደይ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን እና የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ናቸው የተፈራረሙት፡፡
በርካታ የዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘው ፀደይ ባንክ የዲጂታል ጤና ክፍያዎችን የሙከራ ትግበራ ለማስጀመር በጤና ሚኒስቴር ከተመረጡ የፋይናንስ ተቋማት መካከል አንዱ ሆኗል፡፡ በስምምነቱ መሠረትም ባንኩ የዲጂታል ጤና ክፍያዎችን የሙከራ ትግበራ የሚያስጀምር ይሆናል፡፡
ፀደይ ባንክ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ዘርፍ የሞባይል፣ የኢንተርኔት፣ የካርድ እና ሌሎችንም የባንክ አገልግሎቶች ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
ፀደይ ባንክ 62 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሀብት፣ 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል እና 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ካፒታል ያለው ግዙፍ ባንክ ነው፡፡ ከ14 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ባንኩ ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑት ብድር ሰጥቷል፡፡




Leave a Reply