News and Press

የፀደይ ባንኩ አትሌት ዳዊት ቢተው በ1500 ሜትር ውድድር የፍፃሜ ውድድሩን በ1ኛነት አጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ከሰኔ 25/2016 እስከ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብም በውድድሩ በተወሰኑ አትሌቶች አማካኝነት እየተወዳደረ ይገኛል።

በዚህ ውድድር የፀደይ ባንኩ አትሌት ዳዊት ቢተው በ1500 ሜትር 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳልያ አስገኝቷል።

በውድድሩ በበላይነት ያጠናቀቀው አትሌት ዳዊት የክለቡ ባለቤት የሆነው ፀደይ ባንክ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደጋጋሚ እንዲተዋዎቅ ማስቻሉን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ ደሳለው እንዳለው ያደረሰን መረጃ ያመላክታል።

በሌላ ዜና የፀደይ ባንክ አትሌት መቅደስ ሽመልስ የመቻል (የመከላከያ) ስፖርት አዲስ አበባ ከተማ ላይ ከሰሞኑ ባዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የአስፓልት ላይ ውድድር ነው በአንደኛነት ማጠናቀቋ ይታዎሳል።

ፀደይ ባንክ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የራሱን አትሌቲክስ ክለብ በመመስረትና በጀት በመመደብ በርካታ ወጣት አትሌቶች ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉና ሀገርን በተለያዩ መድረኮች እንዲያስጠሩ እያደረገ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *