የጨረታ ማስታዎቂያ
ፀደይ ባንክ (አ.ማ) ለአቶ ጌታቸው አባት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሰንጠረዡ የተዘረዘሩ መኖሪያ ቤቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራጮች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራጮች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፀደይ ባንክ ስም (አ.ማ) በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ...