ፀደይ ባንክ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ጋር የክፍያ አጋርነት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡
ፀደይ ባንክ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱ ፀደይ ባንክ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን የሚሰጠውን የክፍያ እና የርክክብ ስርዓት ለማቀላጠፍ እንዲሁም በመጋዝን ደረሰኝ ብድር ተጠቃሚነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡ የስምምነቱን ፋይዳ በተመለከተ የፀደይ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን እና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድምአገኝ ነገራ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የፀደይ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን ባለሥልጣኑ አገልግሎቱን እያቀረበላቸው ያሉት አርሦ አደሮች እና አምራች የማኅበረሰብ ክፍሎች ወደ ምርት ገበያው መጥተው ምርታቸውን...