News and Press

ፀደይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ለተጎጂዎች በአመልድ ኢትዮጵያ በኩል የሚደርስ ይሆናል። በዚህም መሠረት የፀደይ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ መኮንን የለውምወሰን የ 50 ሚሊዮን ብር ድጋፉን ለአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ ዛሬ ኅዳር 22/03/2016 ዓ.ም በዋናው መሥሪያ ቤት በተካሄደ መርሐ-ግብር አስረክበዋል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ የሰዎች ሞት ጭምር ያስከተለውን የድርቅ እና የረሃብ ችግር ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አስቦ ድጋፍ መሰጠቱን ተናግረዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ እስከ 200 ሚሊዮን ብር ለተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሰዋል።

የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዶ.ር ዓለማየሁ ዋሴ በኩላቸው ፀደይ ባንክ ለተጎዱ ወገኖች ላደረገው ድጋፍ በድርጅታቸውና በተረጂ ወገኖች ስም አመስግነዋል።

በዋግኽምራ እና ሰሜን ጎንደር በድርቁ ምክንያት ከ450 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ያነሱት ዶ.ር ዓለማየሁ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ዕርዳታውን እንደሚያደርሱም ቃል ገብተዋል።

ፀደይ ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ማኅበራዊ ኀላፊነቱን በቀዳሚነት በመወጣት ይታዎቃል። የፀደይ ባንክ ኮርፖሬት ማርኬቲንግ እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ቢራራ በዜ ባንኩ ከዚህ በፊትም ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት ለስፖርት፣ ለትምሕርት፣ ለቅርስ ጥበቃ፣ ተፈናቃይ ወገኖችን ለማቋቋም እና ለታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።

ባንኩ በቋሚነት ለፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ እና ከ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡና የገንዘብ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ እስከሚመረቁ ድረስ ድጋፍ እያደረገም ይገኛል።

• የፀደይ ባንክ ትክክለኛ የዲጂታል ሚዲያ ገፆችን በእነዚህ ሊንኮች ይቀላቀሉ።

•Website: https://tsedeybank-sc.com/

•Telegram:https://t.me/tsedeybanksc

•Twitter: https://twitter.com/TsedeyBankSC

•LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/tsedey-bank-s-c/

•Facebook: https://www.facebook.com/TsedeyBankSC

•TikTok: www.tiktok.com/@tsedeybanksc

•Youtube:https://youtube.com/@TsedeyBank

#TsedeyBank #Bankforall #Banking #BankinginEthiopia #BanksinEthiopia #NBE #NationalBankofEthiopia #ForeignBanksEntrytoEthiopia #BankwithTsedey

#ፀደይባንክ!

#የሁሉምባንክ!

#TsedeyBank!

#Bankforall

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220