News and Press

አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ለፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽነትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የላቀ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማኅበር 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በፓናል ውይይት፣ በአውደ ርዕይ እና በልዩ ልዩ ዝግጂቶች እየተከበረ ነው፡፡

የፀደይ ባንክ ፕሬዚዳንት እና የማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መኮንን የለውምወሰን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ለኢኮኖሚ እና ለማኅበራዊ ልማት ያላቸውን አስተዋጽኦ በሚመለከት ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ለፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽነትና ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማኅበር 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “ማይክሮ ፋይናንስ በዲጂታል ዘመን የፋይናንስ አካታችነት ለሥራ ፈጠራና ለሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ሃሳብ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220