የፀደይ ባንክ አትሌቶች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 5 ኪ.ሜ ውድድር አሸነፉ።
የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ አትሌቶች ዛሬ መጋቢት 07/2017 ዓ.ም በተካሄደው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል። ውድድሩ በየዓመቱ የሚዘጋጅ፣ በርካታ ልምድ ያላቸው እና ጠንካራ ሴት አትሌቶች የሚሳተፉበት ነው። በዚህ የ 5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ውድድር የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ አትሌት ብርነሽ ደሴ 1ኛ፣ አትሌት መቅደስ ሽመልስ ደግሞ 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል። በውድድሩ 2ኛ የወጣችው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌት አበዙ ከበደ ናት። በዚህ ውድድር ባለፈው ዓመት አትሌት ብርነሽ ደሴ 2ኛ፣ አትሌት መቅደስ ሽመልስ ደግሞ 3ኛ በመውጣት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። በርካታ ማኅበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ የሚገኘው...