News and Press

የፀደይ ባንኩ አትሌት በዓለም ሻምፒዮና!

የፀደይ ባንኩ አትሌት ይስማው ድሉ በሰርቢያ ቤልግሬድ እየተካሄደ በሚገኘው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና 4ኛ በመሆን የዲፕሎማ ደረጃ አግኝቷል። አትሌቱ ኢትዮጵያ በቡድን የብር ሜዳልያ እንድታገኝም ከፍተኛውን አስተዋፅዖ አበርክቷል።

ዛሬ በ8 ኪ.ሜትር ወጣት ወንዶች በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በቡድን 2ኛ በመሆን የብር ሜዳልያ እንድታገኝ የፀደይ ባንኩ አትሌት ይስማው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን የቡድን አጋሮቹ ጋር ብርቱ ጥረት አድርጓል።

የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ አትሌቱ ይስማው ድሉ ጥር 05/2016 ዓ.ም በተካሄደው 41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ውድድር ነበር በሰርቪያ ቤልግሬድ ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል ለመወዳደር የተመረጠው፡፡

በበርካታ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ደማቅ ዐሻራ እያሳረፈ የሚገኘው ፀደይ ባንክ 2004 . ጀምሮ የራሱን አትሌቲክስ ክለብ በማቋቋም በርካታ ወጣቶች ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉ እየደገፈ ይገኛል።

አትሌቶቹም ከሀገር አቀፍ ስኬቶች ባለፈ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮችም ኢትዮጵያን ለድል እያበቁ ከሚገኙት ብርቅዬ ልጆቿ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ በዓለም የውድድር መድረኮች ኢትዮጵያን በመወከል አንድ የወርቅ፣ አምስት የነሐስ እና ሁለት የብር፣ በድምሩ ስምንት ሜዳልያዎችን ማስመዝገቡ ይታዎሳል፡፡

በሀገር አቀፍ እና በክልል አቀፍ ውድድሮች ደግሞ 190 የወርቅ፣ 160 የብር እና 152 የነሀስ፣ በድምሩ  502 ሜዳልያዎችን የግሉ ማድረጉ ይታዎሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved