News and Press

ፀደይ ባንክ ቅርንጫፎቹን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እያስፋፋ ነው፡፡

ፀደይ ባንክ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ ተጨማሪ 142 ቅርንጫፎችን መክፈቱን የባንኩ የዲጂታልና ብራንች ባንኪንግ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም የባንኩን ቅርንጫፎች ብዛት 608 ማድረስ ተችሏል፡፡

በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ሆሳዕና፣ ይርጋ ጨፌ፣ ሻሸመኔ እና ሀዋሳ ከተሞች ላይ ቅርንጫፎች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ያስረዱት አቶ ቴዎድሮስ በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ደግሞ ድሬዳዋ፣ ሎጊያና አሳይታ ከተሞች ቅርንጫፎች መከፈታቸውን ገልጸዋል፡፡ በደቡብ ምዕራቡ የሀገሪቱ ክፍል ደግሞ ጅማ፣ ጋምቤላ፣ ሚዛን አማን እና ባኮ ከተሞች ቅርንጫፎች እየተከፈቱ ሲሆን በሰሜኑ መቀሌ ከተማ ላይ ቅርንጫፍ በመክፈት ሥራ እንደተጀመረ ነው የገለጹት፡፡

እንደ አቶ ቴዎድሮስ ገለጻ በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በሸገር ሲቲ ውስጥ እንደ ሰበታ፣ ሱሉልታ እና ለገጣፎ ባሉ ከተሞች ጨምሮ በአጠቃላይ 74 ቅርንጫፎች ተከፍተዋል፡፡

ይህም ‹‹የሁሉም ባንክ!›› የሚለውን መሪ ሀሳብ በተግባር እየኖረ ያለ ባንክ መሆኑን ያሳያል ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ የባንኩን ተደራሽነት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ይበልጥ ለማስፋት እየተሠራ መሆኑን ነው ያሳወቁት፡፡

በዚህም ለደንበኞቻችን ይበልጥ በመቅረብ አገልግሎት መስጠት፣ አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት፣ የሥራ ዕድል መፍጠር እና ሌሎችንም ጥቅሞች ማግኘት እየተቻለ ነው፡፡ ፀደይ ባንክ አዳዲስ በከፈታቸው ቅርንጫፎች ብቻ ከ300 በላይ ሠራተኞችን በመቅጠር የሥራ ዕድል ስለመፍጠሩም አቶ ቴዎድሮ አስታውቀዋል፡፡  

ፀደይ ባንክ ወደ ባንክ ከመሸጋገሩ ከመስከረም 2015 ዓ.ም በፊት 472 የማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፎች እና ከ1000 በላይ ሳተላይት ቅርንጫፎችን በመያዝ በአማራ ክልል ሰፊ የፋይናንስ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር የሚታዎስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved