News and Press

ፀደይ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት ዛሬ ታኅሳስ 19/2016 ዓ.ም ነው፡፡

በደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት የተፈራረሙት የፀደይ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአቬሽን ዩኒቨርሲቲ የሥልጠና ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ካሴ ይማም ናቸው፡፡

አየር መንገዱ የካበተ እና ውጤታማ የደንበኛ አገልግሎት ያለው በመሆኑ ባንኩ ከአስራ ሶስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹን በዘርፉ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያግዝ የፀደይ ባንክ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል፡፡

የተሻለ የደንበኞች አያያዝ ከሌሎች ልዩ እንደሚያደርጋቸው የተናገሩት አቶ ካሴ ይማም ይህም አየር መንገዱንም ውጤታማ አድርጎታል ብለዋል፡፡ ከፀደይ ባንክ ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረትም በደንበኞች አገልግሎት ላይ በትኩረት ሥልጠናዎችን እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል፡፡

ፀደይ ባንክ አጠቃላይ ካፒታሉን 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን፣ አጠቃላይ ሃብቱን ደግሞ 56 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ግዙፍ ባንክ ነው፡፡

Join us on our digital media platforms:

Website (https://tsedeybank-sc.com/)

Telegram (https://t.me/tsedeybanksc)

Twitter (https://twitter.com/TsedeyBankSC)

LinkedIn (https://www.linkedin.com/company/tsedey-bank-s-c/)

Facebook (https://www.facebook.com/TsedeyBankSC)

TikTok (http://www.tiktok.com/@tsedeybanksc)

Youtube (https://youtube.com/@TsedeyBank)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220