News and Press

የፀደይ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለተከበራችሁ የፀደይ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች፤

የፀደይ ባንክ አማ የባለአክሲዮኖች 3ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366፤ 367፤ 370፤371 እና 372 መሠረት ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ሀይሌ ግራንድሆቴል ይካሄዳል፡፡ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን: ሰዓት እና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

ስለ ባንኩ መግለጫ፡-

  • የባንኩ የተፈረመ ካፒታል፡ ብር 9837889000.00
  • የባንኩ የተከፈለ ካፒታል፡ ብር 9833346177.00
  • የባንኩ ዋና የንግድ ምዝገባ ቁጥር ፡  MT/AA/3/0052707/2014
  • የባንኩ የሥራ ፈቃድ ቁጥር: LBB/TM/026/2022      
  • የባንኩ አድራሻ፡አዲስ አበባ ከተማ፣ቂርቆስ ክፍለከተማ፣ ወረዳ07፣ለገሃርመብራት አካባቢአመልድ ህንፃ ከ8 እስከ14 ፎቅ፤ስልክ ቁጥር 0115584133

የ3 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-

  1. ድምጽቆጣሪዎችንመሰየም፤
  2. ምልዓተጉባዔመሟላቱንማረጋገጥ፤
  3. የጉባኤውንአጀንዳዎችማጽደቅ፤
  4. የአክሲዮንዝውውሮችንማሳወቅእናማጽደቅ፤
  5. እ.ኤ.አየ2022/2023 የዳይሬክተሮችቦርድዓመታዊሪፖርትንማዳመጥ እናበሪፖርቱላይተወያይቶመወሰን፤
  6. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የባንኩንየውጭኦዲተርዓመታዊሪፖርትንማዳመጥ እናበሪፖርቱላይተወያይቶመወሰን፤
  7. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የባንኩን የተጣራትርፍአደላደልእናአከፋፈልላይተወያይቶመወሰን፤
  8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን አመታዊ የአገልግሎት ክፍያ (Compensation) እና ወርሃዊ አበል መወሰን፤
  9. ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ባንኩን የሚያገለግሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መሾም፤
  10. የባንኩን 3ኛየባለአክሲዮኖችመደበኛጠቅላላጉባኤቃለ-ጉባኤማፅደቅ፤

ሳሰቢያ፡-

  1. ባለአክሲዮኖችበጉባኤው ለመገኘት ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት፣ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ዋናውን ከፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በውክልና የሚገኙ ከሆነ የወካዩን ባለአክሲዮን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ውክልና መስጠት የሚፈልግ ባለአክሲዮን ከህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጉባዔው ከሚካሄድበት እለት ቢያንስ ሶስት ቀን እስኪቀረው ድረስ  በስራ ሰዓት ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ መንጃ ፈቃድ፣ ወይም ፓስፖርት ይዞ  ለገሃር በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አመልድ ህንፃ 8 ፎቅ ወይም በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ በየትኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  4. ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል በተረጋገጠ እና በጉባዔዎቹ ለመካፈል የሚያስችል የውክልና ስልጣን የተሰጣቸው ወኪልዎ በእለቱ በጉባዔዎቹ ቦታ የውክልና ሰነዱን ኦሪጅናል እና አንድ ፎቶኮፒ ይዘው በመቅረብ ጉባዔዎቹን መሳተፍ ይቻላሉ፡፡
  5. ድርጅትንወክሎየሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ ወይም የማህበሩ ሥራ አስኪጅ መሆኑን የሚረጋግጥ ማስረጃ ወይም የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ወይም ቃለ-ጉባዔ ይዞ መቅረብ ያለበት መሆኑን አልያም በባንኩ የውክልና ቅጽ መሰረት ውክልና የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

የፀደይ ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220