News and Press

ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

ለፀደይ ባንክ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የፀደይ ባንክ አ.ማ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ሐምሌ 16 ቀን 2015 እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባላትን ጥቆማ ይቀበላል፡፡

በመሆኑም፣ የባንኩ ባለአክስዮኖች ለባንኩ የላቀ ውጤት ለማበርከት ብቃት ያላቸውን በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2008 እና 1159/2019/የተሻሻለው በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/71/2019 እና SBB/79/2021 ላይ የተዘረዘሩትን የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩ የቦርድ አባላትን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ እንድትጠቁሙ ጥሪ ያቀርባል፡፡

ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች

  1. የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ፣
  2. ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያለው፣
  3. ዕድሜው 30 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
  4. የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ፣
  5. በዳይሬክተሮች ቦርደ አባልነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፣
  6. በቂ የአመራር ክህሎት ያለው፣
  7. በባንኪንግ/ፋይናንስ/አካውንቲንግ/ማኔጅመንት/ኢኮኖሚክስ/ህግ/በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን/ ኢንቨስትመንት ማኔጅመንት/ኦዲቲንግ/ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የትምህርት ዝግጅትና አግባብነት ያለው የሞያ ልምድ ያለው ቢሆን ይመረጣል፣
  8. በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የዳሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ያልሆነ፣
  9. ሀቀኛ፣ ታማኝ፣ ጠንቃቃ ፣ከሱስ ነፃ እና መልካም ስብእና እና ዝና ያለው በተለይም በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሒሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ እና ተጠቋሚዎች ሥልጣን ላለው ተቆጣጣሪ አካል መስጠት ያለባቸውን መረጃ በመደበቅ፣ ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት፣ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት ባለማሟላት ምክንያት የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን የሚያሳይ ሪከርድ የሌለባቸው መሆን አለበት፡፡
  10. በራሱ ወይም ዳይሬክተር፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የበላይ ኃላፊ በመሆን የሚመራው ድርጅት ላይ በመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሣራ ውሳኔ ያልተሰጠበት፣
  11. በኪሣራ ምክንያት ንብረቱ ለእዳ ማቻቻያ ያልተወሰደበት፣
  12. የባንክ ብድር ባለመክፈል ምክንያት ንብረቱ በሃራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም የቦርድ ዳይሬክተር፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የበላይ ኃላፊ በመሆን የሚመራው ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት ወይም ያልገባበት፣
  13. በቂ ስንቅ/ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሒሳቡ ያልተዘጋበት፣
  14. ቀረጥ እና ግብር ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣
  15. እጩ ተጠቋሚዎች በንግድ ሕጉ እና በኢትዮáያ ብሔራዊ ባንክ በወጡ መመሪያዎች ላይ የተጠቀሱ ሌሎች መመዘኛዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

      ማሳሰቢያ፡-

ፀደይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

  1. በተባዕታይ ፆታ የተገለፀው ለአንስታይ ፆታም ይውላል፡፡
  2. ሴት ተጠቋሚዎች ካሉ ይበረታታሉ፡፡
  3. ጥቆማው በውክልና የቀረበ ከሆነ ውክልናው ጥቆማውን ለማቅረብ የሚያስችል ሆኖ የውክልና ፎቶ ኮፒው ከመጠቆሚያው ቅጽ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. ጠቋሚዉ ባለአክሲዮን ግለሰብ/ማህበር ወይም ድርጅት የተጠቋሚውን ፈቃደኝነት አስቀድሞ ማረጋገጥ አለበት፡፡
  5. የመጠቆሚያ ቅፁን ስታዲየም በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋናው መ/ቤት 8ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ፤ በባንኩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ወይም ከባንኩ ድረ ገፅ www.tsedeybank-sc.com ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ለጥያቄና ማብራሪያ ስታዲየም በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋናው መ/ቤት 8ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ +251115580180/+251912490400 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  7. የመጠቆሚያ ቅፁ በአግባቡ ተሞልቶና ተፈርሞበት ማህበር/ ድርጅት ከሆነ ደግሞ ማህተም ተደርጎበት በባንኩ ዋናዉ መስርያ ቤት 8ኛ ፎቅ የዳይሬክተሮች ቦርደ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ፅ/ቤት፤በባንኩ ሁሉም ቅርንጫፎች ወይም በኮሚቴው የኢሜል አድራሻ tsb.bod@tsedeybank.com.et እና yibeltalejigu@tsedeybank-sc.com ወይም በፀደይ ባንክ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 9630 “ለፀደይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ፅ/ቤት” መላክ ይቻላል፡፡
  8. የቅፁ መመለሻ የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ነው፡፡
  9. ከጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡም ሆነ የሚደርሱ ጥቆማዎችም ተቀባይነት የላቸውም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220