News and Press

የፀደይ ባንክ አትሌት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ውድድር መወከል የሚያስችላትን ውጤት አስመዘገበች።

የፀደይ ባንክ አትሌት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ውድድር መወከል የሚያስችላትን ውጤት አስመዘገበች።

በ42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ውድድር የፀደይ ባንክ አትሌት መቅደስ ሽመልስ በ10 ኪ.ሜ አዋቂ ሴቶች 4ኛ በመሆን አጠናቅቃለች።

ዛሬ ጥር 25/2017 ዓ.ም በተካሄደው ውድድር ያስመዘገበችው ውጤትም ኢትዮጵያን በአሕጉር አቀፍ ውድድር መወከል እንደሚያስችላት የክለቡ ሥራ አስኪያጅ ደሳለው እንዳለው ያደረሰን መረጃ ያመላክታል።

አትሌት መቅደስ ሽመልስ

አትሌት መቅደስ ሽመልስ የመቻል (የመከላከያ) ስፖርት ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ላይ ባዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የአስፓልት ላይ ውድድር በአንደኛነት ማጠናቀቋም ይታዎሳል።

በርካታ ማኅበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ የሚገኘው ፀደይ ባንክ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የራሱን አትሌቲክስ ክለብ በመመስረትና በጀት በመመደብ በርካታ ወጣት አትሌቶች ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉና ሀገርን በተለያዩ መድረኮች እንዲያስጠሩ እያደረገ ይገኛል።

የፀደይ ባንክ አትሌት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ውድድር መወከል የሚያስችላትን ውጤት አስመዘገበች።

የሁሉም ባንክ!
Bank for all!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *