News and Press

የፀደይ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለተከበራችሁ የፀደይ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች፤

የፀደይ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ (የተደገመ) በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366፤ 367፤ 370፤371 እና 372 መሠረት ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ሸራተን ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን: ሰዓት እና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

ስለባንኩ መግለጫ:-

  • የባንኩ የተፈረመ ካፒታል፡                                    ብር 9,837,889,000.00
  • የባንኩ የተከፈለ ካፒታል፡                                      ብር 9,833,346,171.87
  • የባንኩ ዋና የንግድ ምዝገባ ቁጥር ፡                            MT/AA/3/0052707/2014
  • የባንኩ የሥራ ፈቃድ ቁጥር:                                    LBB/TM/026/2022
  • የባንኩ አድራሻ፡ አዲስ አበባ ከተማ፣ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07፣ለገሃር መብራት አካባቢ አመልድ ህንፃ ከ8 እስከ 14 ፎቅ፤ስልክ ቁጥር 0115584133

4 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡

  1. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥ እና በሪፖርቱ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  2. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የባንኩን የውጭ ኦዲተር ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥ እና በሪፖርቱ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  3. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የባንኩን የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  4. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን አመታዊ የአገልግሎት ክፍያ (Compensation) እና እ.ኤ.አ የ2023/2024  ወርሃዊ አበል መወሰን፤
  5. እ.ኤ.አ የ2023/2024 የባንኩን የውጭ ኦዲተር ሹመት እና የአገልግሎት ክፍያ ማፅደቅ፤

ማሳሰቢያ:-

  1. ባለአክሲዮኖች በጉባኤው ለመገኘት ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት፣ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ዋናውን ከፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በውክልና የሚገኙ ከሆነ የወካዩን ባለአክሲዮን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ውክልና መስጠት የሚፈልግ ባለአክሲዮን ይህ ማስታዎቂያ ከተነገርበት ቀን ጀምሮ ጉባዔው እስከሚካሄድበት ቢያንስ ሶስት ቀን እስኪቀረው ድረስ በስራ ሰዓት ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ መንጃ ፈቃድ፣ ወይም ፓስፖርት ይዞ  ለገሃር በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አመልድ ህንፃ 8 ፎቅ የፀደይ ባንክ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል  በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  4. ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል በተረጋገጠ እና በጉባዔዎቹ ለመካፈል የሚያስችል የውክልና ስልጣን የተሰጣቸው ወኪልዎ በእለቱ በጉባዔው ቦታ የውክልና ሰነዱን ኦሪጅናል እና አንድ ፎቶኮፒ ይዘው በመቅረብ ጉባዔውን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  5. ድርጅትን ወክሎ የሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ ወይም የማህበሩ ሥራ አስኪጅ መሆኑን የሚረጋግጥ ማስረጃ ወይም የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ወይም ቃለ-ጉባዔ ይዞ መቅረብ ያለበት መሆኑን ካለዚያም በባንኩ የውክልና ቅጽ መሰረት ውክልና የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

የፀደይ ባንክ .

የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *