እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን የመጠቆሚያ ጊዜ ለአንድ ሳምንት ተራዘመ፡፡
ለፀደይ ባንክ ባለ አክሲዮኖች በሙሉ
የፀደይ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ከሐ ምሌ 16/2015 እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እየተቀበለ እንደሚገኝ ማሳዎቁ ይታዎሳል፡፡
ባለአክሲዮኖች ባቀረቡት ተደጋጋሚ የይራዘምልን ጥያቄ መሠረት የጥቆማ ማቅረቢያ ጊዜውን እስከ ጥቅምት 24/2016 ያራዘመ መሆኑን አስመራጭ ኮሚቴው ያሳዉቃል፡፡
በመሆኑም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2008 እና 1159/2019 በተሻሻለው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB 71/2019 እና SBB 79/2021 የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩ የቦርድ አባላትን በተጠቀሰው ጊዜ ብቻ እንድትጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው ጥሪ ያቀርባል፡፡
የመጠቆሚያ ቅጹን ከባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ወይም ከባንኩ ድረገጽ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ቅጹ በአግባቡ ተሞልቶና ተፈርሞበት በባንኩ ዋና ጽ.ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፎች ወይም በኢሜል አድራሻ TSB.BOD@TSEDEYBANK.COM ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 9630 ለምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ጽ.ቤት መላክ ይችላሉ፡፡
ከጥቅምት 24/2016 በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
የፀደይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ
Leave a Reply