ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የፀደይ ባንክን የዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የፀደይ ባንክን የዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
ፀደይ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ-ሰንጋ ተራ ላይ እያስገነባ ይገኛል፡፡
የባንኩ ባለ 37 ወለል ሕንጻ የግንባታ ሂደትንም ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ዛሬ ጥር 17/2017 ዓ.ም ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝታቸው በኋላም ከባንኩ የማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያይተዋል።
የፀደይ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት አጠቃላይ የቦታ ስፋት 4,024 ሜትር ስኩዌር ሲሆን ግንባታው ያረፈበት ቦታ ደግሞ 3,220 ሜትር ስኩዌር ይሸፍናል፡፡
የፀደይ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልገው ይጠበቃል፡፡
ፀደይ ባንክ በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙትን ጨምሮ በአጠቃላይ 247 ሕንጻዎች አሉት፡፡
እንወዳጅ!
Telegram: https://t.me/tsedeybanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/tsedey-bank-s-c/
Facebook: https://www.facebook.com/TsedeyBankSC
TikTok: http://www.tiktok.com/@tsedeybanksc
Twitter: https://twitter.com/TsedeyBankSC
YouTube: https://youtube.com/@TsedeyBank



የሁሉም ባንክ!
Bank for all!
Leave a Reply