News and Press

የፀደይ ባንኩ አትሌት ኢትዮጵያን ወክሎ በዓለም መድረክ ይወዳደራል።

የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ አትሌቱ ይስማው ድሉ ዛሬ ጥር 05/2016 ዓ.ም በተካሄደው 41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ውድድር ማጣሪያውን አልፏል።

በመሆኑም አትሌቱ በሰርቪያ ቤልግሬድ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል ለመወዳደር ተመርጧል።

አትሌቱ በ8 ኪሎ ሜትር የወጣት ወንዶች ውድድር ሚኒማ በማሟላቱ ነው ኢትዮጵያን በዓለም አገር አቋራጭ ውድድር ለመወከል የተመረጠው።

በበርካታ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ደማቅ አሻራ እያሳረፈ የሚገኘው ፀደይ ባንክ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የራሱን አትሌቲክስ ክለብ በማቋቋም በርካታ ወጣቶች ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉ እየደገፈ ይገኛል።

አትሌቶቹም ከሀገር አቀፍ ስኬቶች ባለፈ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮችም ኢትዮጵያን ለድል እያበቁ ከሚገኙት ብርቅዬ ልጆቿ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ በዓለም የውድድር መድረኮች ኢትዮጵያን በመወከል አንድ የወርቅ፣ አምስት የነሐስ እና ሁለት የብር በድምሩ ስምንት ሜዳልያዎችን ማስመዝገቡ ይታዎሳል፡፡

በሀገር አቀፍ እና በክልል አቀፍ ውድድሮች ደግሞ 190 የወርቅ፣ 160 የብር እና 152 የነሀስ፣ በድምሩ  502 ሜዳልያዎችን የግሉ ማድረጉ ይታዎሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *