News and Press

የፀደይ ባንክ አትሌት መቅደስ ሽመልስ በ10,000 ሜትር ውድድር የብር ሜዳልያ አስገኘች።

54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተጀምሯል፡፡

 በዚህ ውድድር ዘጠኝ የፀደይ ባንክ አትሌቶች በ3,000 ሜትር መሰናክል፣ በ5,000 ሜትር፣ በ10,000 ሜትር እና በ1,500 ሜትር ውድድሮች ይሳተፋሉ፡፡

በመክፈቻው እለት በተካሄደው የ10,000 ሜትር ውድድርም የፀደይ ባንክ አትሌት መቅደስ ሽመልስ በ2ኛነት አጠናቅቃለች፡፡

በውድድሩ ዙሩን በማክርር ከፍተኛ ፉክክር ያደረገችው አትሌት መቅደስ፣ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ባለቤት ሆናለች፡፡

አትሌት መቅደስ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ውድድሮች ላይ በአሸናፊነት በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለች ብርቱ ተወዳዳሪ አትሌት መሆኗ ይታዎሳል፡፡

ፀደይ ባንክ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የራሱን አትሌቲክስ ክለብ በመመሥረት እና በጀት በመመደብ በርካታ ወጣት አትሌቶችን በማፍራት ላይ ይገኛል፡፡ አትሌቶቹም በተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያን እያስጠሩ እንደሚገኙ ይታዎቃል፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የተጀመረው ይህ ውድድር እስከ ግንቦት 03/2017 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *