News and Press

የፀደይ ባንክ አትሌት ይስማው ድሉ በቡዳፔስቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይወዳደራል፡፡

የፀደይ ባንክ አትሌት ይስማው ድሉ ኢትዮጵያን በመወከል ለቡዳፒስቱ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10,000 ሜትር ለመሮጥ የሚያስችለውን ሚኒማ በማሟላት መመረጡ ይታዎሳል፡፡

በዚህም መሠረት በሀንጋሪ ቡዳፔስት ከነሐሴ 13 እስከ ነሐሴ 21 ዓ.ም በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በመወከል ይወዳደራል፡፡

የውድድሩ መርሐ ግብር እንደሚያሳየውም አትሌት ይስማው ኢትዮጵያን ወክሎ ነሐሴ 14/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1:25 በዓለማችን ካሉ ምርጥ አትሌቶች ጋር ይወዳደራል።

የፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ በዓለም የውድድር መድረኮች ኢትዮጵያን በመወከል አንድ የወርቅ፣ አምስት የነሐስ እና ሁለት የብር በድምሩ ስምንት ሜዳልያዎችን ማስመዝገቡ ይታዎሳል፡፡

በሀገር አቀፍ እና በክልል አቀፍ ውድድሮች ደግሞ 190 የወርቅ፣ 160 የብር እና 152 የነሀስ፣ በድምሩ 502 ሜዳልያዎችን የግሉ አድርጓል፡፡

ፀደይ ባንክ የአትሌቲክስ ክለቡን ሙሉ ወጪ ከመሸፈን ባለፈ በርካታ ማኅበራዊ ኀላፊነቶችን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ድል ለባንካችን አትሌት!
ድል ለመላው የኢትዮጵያ አትሌቶች!

  • የፀደይ ባንክ ትክክለኛ የዲጂታል ሚዲያ ገፆችን በእነዚህ ሊንኮች ይቀላቀሉ።
    •Website: https://tsedeybank-sc.com/
    •Telegram:https://t.me/tsedeybanksc
    •Twitter: https://twitter.com/TsedeyBankSC
    •Facebook: https://www.facebook.com/TsedeyBankSC
    •Youtube:https://youtube.com/@TsedeyBank

ፀደይባንክ!

የሁሉምባንክ!

TsedeyBank!

BankForAll

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *