News and Press

ፀደይ ባንክ የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቶችን በይፋ አስጀመረ፡፡

ባንኩ የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ማስጀመሩን አስመልክቶ ዛሬ ታኅሳስ 10/2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

የፀደይ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን ባንኩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሠራ  መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመሩት የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቶችም የዚህ አካል መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱ ዘመናዊነትን የተላበሰ ስለመሆኑ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ደንበኞች ራሳቸው መመዝገብ የሚችሉበት፣ ከምስጢር ቁጥር በተጨማሪ በአሻራ እና በባዮሜትሪክስ አገልግሎት መሥጠት የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም ባንኩን ተወዳዳሪ የሚያደርጉ እና የደንበኞችን ፍላጎት የሚያሟሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚያስተዋውቅም ነው የገለጹት፡፡

ደንበኞች በማንኛውም ዓይነት ሞባይል ወደ *616# በመደወል ወይም የፀደይን ሞባይል ባንኪንግ አፕሊኬሽን ከ App Store እና Play Store በማውረድ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ አገልግሎቶቹን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጧል፡፡

በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶቹ ወደ ራስዎ የሂሳብ ቁጥር እና ወደ ሌላ የፀደይ ባንክ የሒሳብ ቁጥር ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ከፀደይ ባንክ ወደ ሌሎች ባንኮች ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ከቴሌ ብር መቀበልም ሆነ ወደ ቴሌ ብር ማስተላለፍ፣ የሒሳብ መግለጫ መረጃዎን መከታተል፣  ቀሪ ሒሳብዎን ማዎቅ፣  ዓየር ሰዓት መሙላት እንደሚቻልና በቅርብ ቀን ደግሞ ሌሎች በርካታ  አገልግሎቶች እንደሚተዋዎቁ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የፀደይ ባንክ ብራንድ አምባሳደር አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ በበኩሉ የሁሉም ባንክ የሆነው ፀደይ ለማኅበረሰቡ ቅርብ ለመሆንና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለመስጠት በሚሠራቸው ሥራዎች አብሮ በመሆኑ ደስተኛ መሆኑን ገልጧል፡፡

በ1988 ዓ.ም የገጠር ብድር አገልግሎት በሚል ስያሜ ሥራውን ጀምሮ፣ በ1989 ዓ.ም ወደ አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የተሸጋገረው የአሁኑ ፀደይ ባንክ ከመስከረም 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በይፋ ወደ ባንክነት መሸጋገሩ ይታዎቃል፡፡

ፀደይ ባንክ አጠቃላይ ካፒታሉ 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ሃብቱ  ደግሞ 55 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር አልፏል፡፡

ከ 13 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ፀደይ ባንክ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑት ደንበኞቹ ብድር በመስጠት ለሕልማቸው እውን መሆን በተግባር አለኝታነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220