News and Press

ፀደይ ባንክ በሽግግር ላይም ሆኖ ጥሩ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገለፀ።

ባንኩ የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2016 እቅድ ትውውቅ አካሂዷል።

ከሐምሌ 05-06/2015 ዓ.ም በተካሄደው የአፈፃፀም እና የእቅድ ትውውቅ ውይይት የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የሁሉም ዲስትሪክቶች ሥራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል።

ባንኩ በሽግግር ላይ ሆኖም ጥሩ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ፕሬዝዳንቱ አቶ መኮንን የለውምወሰን ገልፀዋል። የብድር እና የገንዘብ ፍሰት ጤናማነትን በማስጠበቅ በኩልም በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ነው የተመላከተው።

ፀደይ ባንክ በአገልግሎት እና በፕሮዳክቶቹ ልዩ ባንክ የመሆን እቅዱን ለማሳካት እንደሚሠራም ፕሬዝዳንቱ አመላክተዋል።

በአዲሱ እቅድ ደግሞ የገበያ አማራጮችና ድርሻውን ማሳደግ፣ የፀደይ መለያ የሚሆኑ አዳዲስ ፕሮዳክቶችን እና ዲጂታል የባንክ አገልግሎት መስጫ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት፣ ፈጣንና ደንበኞችን የሚያረካ አገልግሎትን ማስቀጠል ትኩረት ከሚሰጥባቸው ዐበይት ተግባራት መካከል እንደሚሆኑ ነው ያመላከቱት።

ፀደይ ባንክ ያለውን ሠፊ ተደራሽነት፣ መልካም ሥም እና የደንበኞች ብዛት በማሳደግ የተቀማጭ ገንዘብ አቅሙን አሁን ካለበት በላይ ማሳደግም በበጀት ዓመቱ ትኩረት እንደሚደረግባቸው ነው የተጠቀሰው።

ፀደይባንክ!

የሁሉምባንክ!

TsedeyBank!

BankForAll

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220