News and Press

ፀደይ ባንክ ከአሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ ለመሥራት ተፈራረመ፡፡

ፀደይ ባንክ እና አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ አብሮ ለመሥራት ዛሬ (ሰኔ 16/2015ዓ.ም) በኢንተርኮንቲነታል ሆቴል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመዋል፡፡

ስምምቱ የሥራ እድል ፈጠራን የሚያግዝ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ፀደይ ባንክ  በኮሌጁ ሰልጥነው ለሚወጡ ወጣቶች በራሳቸው የፈጠራ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ስምምነቱ የራሳቸውን የሥራ ዕድል ለሚፈጥሩ ወጣቶች ድጋፍ በማድረግ የሥራ አጥነት ቁጥርን ለመቀነስ ሚናው ከፍ ያለ  ስለመሆኑ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ተገልጧል፡፡

ፀደይ ባንክ ከተሰማራበት የፋይናንስ አገልግሎት ባለፈ ማኅበረሰብን የሚጠቅሙ እና ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት እያከነወነ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡ የዛሬው ስምምነትም የዚሁ አንዱ ማሳያ ማሳያ ነው፡፡ 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220