News and Press

የፀደይ ባንክ አስደናቂ ማኅበራዊ ኀላፊነቶችን እናስተዋውቅዎ!

ፀደይ ባንክ በታቀደ እና ማኅበረሰብን ተጠቃሚ ማድረግን ዓላማ ባደረገ መልኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ያውቃሉ?

  1. ባንኩ በብድር እና ቁጠባ ተቋምነት ከተመሠረተበት ከሩብ ክፍለ ዘመናት በፊት ጀምሮ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
  2. ለአብነትም፡- ደጋፊ ያጡ ተማሪዎችን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ “ብቁ” በሚል ስያሜ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲ እስከሚመረቁ ድረስ እያስተማረ ለሥራ  አብቅቷል፤ ይህ ኃላፊነት አሁንም ቀጥሏል፡፡ ተማሪዎቹን የሚመርጠውም ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ በጀመረባቸው (ሰቆጣ፣ ሐይቅ፣ ጨፋ፣ ዱርቤቴ፣ ቆቦ እና አምበሳሜ) ነው፡፡
  3. ከጥቅምት 2004 ዓ.ም ማለትም ከ10 ዓመት በፊት ደግሞ አትሌቲክስ ክለብ አቋቁሞ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን እየደገፈ ይገኛል። “ፀደይ ባንክ” አትሌቲክስ ክለብ በአሁኑ ወቅት 50 አትሌቶች፣ 2 አሰልጣኞች እና 1 ሥራ አስኪያጅ አለው። ፀደይ ባንክ በዚህ ክለብ አማካኝነት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች በበጎ እያስጠራ፣ ለሀገርም ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ ለአብነትም፦ ክለቡ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያን በመወከል 1 የወርቅ፣ 5 የብር፣ 2 የነሀስ ፣ በድምሩ 8 ሜዳልያ አስገኝቷል። በሀገር አቀፍ እና በክልል አቀፍ ውድድሮች ደግሞ 190 የወርቅ፣ 160 የብር እና 152 የነሀስ፣ በድምሩ  502 ሜዳልያዎችን የግሉ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም 52 ዋንጫዎችን በተለያዩ ውድድሮች አግኝቷል። ክለቡ ይህን ስኬት እንዲያስመዘግብ እና ወጣቶች ሕልማቸውን እውን እንዲያደርጉ በማስቻል በኩል የፀደይ ባንክ  ሙሉ የበጀት ድጋፍ ትልቅ ፋይዳ አለው።
  1. ፀደይ ባንክ ለበርካታ ሺኅ ዘመናት ከባህላዊ አስተራረስ ዘዴ ያልተላቀቀው ግብርና እንዲዘምንና የአርሦ አደሮች ሕይዎት እንዲሻሻል ለማድረግ ለአርሦ አደሮች የትራክተር መግዣ የረዥም ጊዜ ብድር በማመቻቸት ለዓመታት እየሠራ ይገኛል፡፡
  2. ለእግር ኳስ እድገትም በየጊዜው በርካታ ሚሊዮን ብር ድጋፍ እያደረገ የማኅበረሰብ አለኝታነቱን በተግባር እየገለጠ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡
  3. በትምህርት ዘርፉም በርካታ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለአብነትም፡- የትምህርት ቤት ግንባታ ብዙም ባልተስፋፋበት ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ውስጥ በ 13 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስገንብቶ ብዙዎችን ከትምሕርት ብርሃን ጋር አገናኝቷል፡፡
  4. ፀደይ ባንክ በሀገር አቀፍ እና ክልል አቀፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች፣ በቅርስ ጥበቃ እና ጥገና ሥራዎች፣ ጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም በመከላከል ሥራ፣ ዜጎች በተፈጥሯዊ እና በሠው ሠራሽ አደጋዎች ለችግር ሲጋለጡ ቀድሞ በመድረስ በየዓመቱ በርካታ ሚሊዮን ብር ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ የሁሉም ባንክ ነው፡፡

#ፀደይባንክ!

#የሁሉምባንክ!

#TsedeyBank!

#Bankforall!

የፀደይ ባንክ ትክክለኛ የዲጂታል ሚዲያ አማራጮችን ከታች ባሉት ሊንኮች ይከታተሉ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *