News and Press

ፀደይ ባንክ ከ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታች ሽልማት ሰጠ፡፡


ፀደይ ባንክ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች 6 መቶ ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

 ሽልማቱን የሰጠው ታኅሳስ 14/2016 ዓ.ም ነው፡፡
ከዚህ ባሻገር ባንኩ ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል በከፍተኛ ውጤት ላለፉና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምሕርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ ድጋፍ በማድረግ በርካታ ጎበዝ ተማሪዎች ሕልማቸውን እውን እዲያደርጉ እየሠራ መሆኑም ይታዎቃል፡፡ ይህ መርሐ-ግብር ‹‹ብቁ›› የሚል ስያሜ ያለውና ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኝ ነው፡፡

ለትምሕርት ዘርፉ ድጋፍ በማድረግ ደማቅ አሻራ ያለው ፀደይ ባንክ የትምህርት ቤት ግንባታ ብዙም ባልተስፋፋበት ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ውስጥ በ 13 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስገንብቶ ብዙዎችን ከትምሕርት ብርሃን ጋር ማገናኘቱም የሚታዎስ ነው፡፡

ፀደይ ባንክ በዚህ ወቅት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሰሜን ጎንደር እና በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታዎሳል፡፡

የሁሉም ባንክ የሆነው ፀደይ ባለፈው ዓመት ብቻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ለተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ድጋፍ አድርጓል፡፡

Join us on our digital media platforms:

Website: https://tsedeybank-sc.com/
•Telegram: https://t.me/tsedeybanksc
•Twitter: https://lnkd.in/eDgMWbRK
•LinkedIn: https://lnkd.in/e9YuyCN9
•Facebook: https://lnkd.in/e7sCsQrq
•TikTok: https://lnkd.in/euNMCiFJ
•Youtube: https://lnkd.in/eMyfh2my


#ፀደይባንክ!
#የሁሉምባንክ!
#TsedeyBank!
#Bankforall

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


Feedback

    Copyright © 2023 Tsedey Bank S.C. | All Rights Reserved

    Call Center / ነጻ የጥሪ ማዕከል፡ 8220